ትውልድ ፈታኝ ቀውጥ !!!

0
99
“ ” በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ እንዲሉ፣ በድረቅ የደቀቀው ህዝባችን፥ በኣሁኑ ወቅት ደግሞ በግጭቶች ሳብያ
እያለቀ ነው። ሃገር ከባድ ቀውጥ ውስጥ ገብታለች። በእርስበርስ ግጭቶች ሳብያ ከድንበሩ ጀምሮ ማህሉ
ድረስ ባለው ህዝባችን ላይ የሞትና የመቁሰል ኣደጋዎች እየደረሱ ናቸው። በገፍ መፈናቀልና ንብረት
መውደም ኣብሮ እየተከተለ ነው። ግጭቱ ባልደረሰባቸው ኣከባቢዎች ጭንቅና ፍርሃት ኣይለዋል። ይህ
እየተሰራጨ ያለው ክፉ ክስተት ማቆምያ ካልተበጀለት ሃገር– ኣልባ ሊያደርገን ይችላል። ቀውጡን የፈጠረው
የህወሓት/ ኢህኣዴግ ገዢ መደብ ለመሆኑ ኣጠያያቂ ኣይደለም። ይህ ሓላፊነት የማይሰማው ኣምባገነን ቡድን
ገና ከጅምሩ የወጠናቸው ደንባራና ስግብግብ ፖሊሲዎች እንዲሁም ኣረመንያዊ የኣገዛዝ ዘይቤዎች ኣሁን
ከምንገኝበት ኣረንቋ ውስጥ ከቶናል። ኣጠቃላይ ኣቅጣጫው መላው ህዝቡን እርስበርስ የሚያፋጅ፥ ሃገርን
በጎጥ ጭምር የሚበታትን ለመሆኑ በኣራቱም መኣዝናት ከሚሰማው የድረሱልን ጩኸት መገንዘብ
ኣያዳግትም።