የሐብታሙ አያሌው የእስርቤት መከራን ስናስታውስ

0
48

ለዴሞክራሲ የሚደረገው ትግል ከተጀመረ አምስት አስርተ አመታት አስቆጥሯል። በነዚህ አመታት በጣም ብዙ ቁጥር ያላቸው የአገሪቱ ታጋዮች አይቀበሉ ግፍን ተቀብለዋል። ሆኖም የነዚያ ታጋዮች መከራ እና ንጹህ ደም ገና የታሰበለትን ግብ መምታት አልቻለም። አሮጌው ጨቋኝ በአዲሱ ይተካ እና ያለፈውን የሚያስንቅ እየሆነ ወንጀል እና ወንጀለኛ ለፍርድ ሳይቀርቡ ብርቅየ የሕዝብ ልጆች ግን አፈር ለብሰዋል። ገሚሶቹ የምድር ሴኦል ተቀብለዋል። የሰው ልጅ ሊደረግ የማግባውን ያውም በራሱ ዜጋ ሲደረግበት አይተናል። የዚያ ትውልድ የማሰቃያ የጨለማ ቤቶችን እና የ 8 ቁጥር የአንጠልጥሎ ግርፋትን፣ እውሀ ከደም የተቀላቀለበት የሞላ በርሚል ውስጥ አንገት እንዲቀበር ሆኖ የእንጥልጥል ግርፋቱ ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ያውም አገር፣ ወገን ለሚወዱ እና ለአገር ለወገን ማንኛውንም እዳ ለመቀበል ዝግጁ ለሆኑ እንደ ጸበል ጻዲቅ ሲዳረስ ማየት ያውም አንድ ትውልድ ሳያልፍ የሚገርም ነው። ያሳዝናልም።

mengestu musi የሐብታሙ አያሌው የእስርቤት መከራን ስናስታውስ