የተጀመረው የፋኖዎች ህብረት መሳካት ለአማራ ህዝብ መከራ ማጠር ዋነኛው ጉዳይ ነው !!!!
ለ30 ዓመታት ብሄርተኞች ስልጣን ይዘው ካደረሱበት ስቃይ እና ዘር መርጦ የማጥፋት ጥቃት እራሱን ለመከላከል ባለመቻሉ የደረሰበት ግፍ በትውልድ እየተከፈለ ይገኛል ::
የአማራ የሶስት አስርተ ዓመታትን ትውልድ በየ አስር ዓመት ከፍለን ሶስት ትውልድ ብለን ስኪቱን እና ጉዳቱን ብንጠይቅ መልሱ ግልፅ ነው::
“”………””
*ሶስቱም ትውልድ የተደራጀ መሪ ድርጅትም አልነበረውም መሪም የለውም
* በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ስልጣን ጭልጥ ያለ ባሪያ ታዛዥ ተገዥ ሆኗል
* በግለሰብ ስኬት በሃብት እና በአካባቢ መሰረተ ልማት የመጨረሻ ነው
* በአለፋት 38 ዓመታት በአማራ ህዝብ ክልል የጤና የመንገድ የፋብሪካ የገጠር እና ከተማ የመንገድ ትስስር ሆን ተብሎ እንዳይሞከር እንዳይታሰብ ተደርጎል
* በ2018 የመንግስት የበጀት ምደባ ብቻ በርካታ ጦርነት የሚፈፀምበት የአማራ ክልል ከኦሮሞ ክልል በጀት በግማሽ ያነሰ እንዲመደብለት ሆኗል
* በአዲስ አበባ አማራ ከስሩ እንዲነቀል ዋና ዋና ነገሮች ተሰርተው አልቀው አማራን አአ አለማስገባት ብቻ ሳይሆን መሰረቱን መንቀሉን ሰርተው ጨርሰውታል 67% አማራ የሚኖርባት አ.አ ዛሬ ለአማራ ሲዖል ሆናለች
*በመከላከያ ፣ በፖሊስ ፣ በአድማ ብተና ፣በፌድራል ፀጥታ በከፍተኛ ቁጥር ታፍሶም ተገዶም ወዶም የሚመደበው 65%ቱ አማራ ነው
* ንብረቱ የሚቀማው በአዲስ አበባ በናዝሬት በአሰላ በድሬድዋ በወለጋ በአማራ ክልል ቤቱ እየፈረሰ ከስራ እየተባረረ ስነልቦናው ተሸናፊ እና ተስፋ ቢስ እየተደረገ ያለው አማራው ነው
* በኪነ ጥበብ በጋዜጠኝነት በቤሮወች የባለሞያ ሰራተኛው ቢያንስ 55%ቱ አማራ ሆኖ እያለ ተደራጅቶ አመራር የሚሰጥ ድርጅት ስሌለለው በተመደበበት ቦታ የውስጥ አርበኛ ሆኖ መታገል እየቻለ የሚያታገለው አመራር እና ድርጅት ሊያገኝ አልቻለም።
* ስለዚህ ዛሬ በፈጣሪ ድጋፍ ታዳጊ የአማራ ወጣቶቻችን በባዶጃቸው ወጥተው የተደራጀውን የመንግስት ጦር አፍርሰው አስተማማኝ የአማራ መከላከያ በሆኑበት በዚህ ወርቅ ጊዜ
* ከዩንቨርስቲ አስተማሪነት ከዶክተርነት ከኮለኔልነት ከገበሬነት ከነጋዴነት ከተማሪነት በፈቃድ እራሱን ተራ የፋኖ ወታደር አድርጎ በጓደኛው ወይም በታናሹ የሻለቃ የብርጌድ የክፍለጦር የእዝ አዛዥነት ስር ሆኖ ወዶ ዝቅ ብሎ የሚታገል ጨዋ አላማ ያለው ጦር ይዘህ አንድ ሆኖ መምራት የማይችል የፋኖ አመራርን አምርረን ልንታገለው በስም ጠርተን ልሞግተው ጫፍ ላይ ደርሰናል::
አሁን የተጀመረው አንድነት ከላይ በዘረዘርኳቸው አማራዊ ምክኔያቶች አስገዳጅነት እንዲሳካ የሁላችንም ሃቀኛ ድጋፍ እና ተሳትፎ ግድ ይለናል!!!
የዕዝ ዓመራሮች ተባበሩ ወይም ስልጣን በአስቸኳይ ልቀቁ የአማራ ህዝብ የወቅቱ ታሪካዊ ጥሪ ነው!!!
አበበ በለው ነኝ
ለአማራ አንድነት ጨርሶ ማይደክመኝ !!!!



